"የእለት ተዕለት ተግባራችን የማንነታችን ነፀብራቅ ነው"

 


ሰዓት እንደዚህ እጥር ባለበት ዘመን ሁሉም ሰው 24 ሰዓት አልበቃኝም ጊዜ የለኝም በሚልበት ዘመን የተለያዩ አይነት መፅሐፍት ስለ habit ስለ ልምድ ተፅፈዋል Atomic habits, the power of habits, discipline equals freedom የመሳሰሉ መፅሐፍት ተፃፈውልናል እነዚህ መፅሐፍት አሁን አሁን በአማርኛ እየተተረጎሙ ብዙ አነቃቂ የሚባሉ ሰዎች podcast, youtube, እንሰማቸዋለን ስለዚህ አስኪ እኔ ደግሞ እንደ አንድ ዘበናይ ሴት አለኝ የምለውን ጥሩ habit ወይንም ልምድ ምንድን ነው? መጥፎስ ልማዴ ምንድን ነው? የሚሉትን ነገሮች መመዝገብ ጀመርኩኝ ስለዚህ ጥሩ ናቸው ያልኩአቸውን እና በጣም ጎበዝ ነኝ ለካ እንደዚህም አደርጋለሁ ይሄንን ከሌላ ሰው ጋር share ባደርገው ወይም ባካፍለው ሌሎች ትምርት ሊያገኙበት ይችላሉ ወይንም ሊለማመዱበት ይችላሉ ብዬ አሰብኩኝ

1) ሁልጊዜ ማታ ማታ ሁሉንም ነገር ከጨረስኩ በሁአላ ለግማሽ ሰዓትም ቢሆን ለመዝናናት neflex, youtube ወይንም ሌላ ነገር ቁጭ ብዬ አያለሁ. ይህን በማደርግበት ጊዜ ቁጭ የምልበት ሶፋ ላይ ሶፋውን የማለብሰው ቆንጆ የሚመቸኝ ለስላሳ እንደ ጋቢ አይነት አለኝ ሶፋውን አልብሼ እኔ ደግሞ ከላይ የምለብሰው አለኝ Special ትራስም አለችኝ ስለዚህ ልክ ፊልሙ አልቆ ወደ መኝታ ስሄድ በምንም ተአምር እዛው ትቼው አልሄድም ወዲያውኑ አጣጥፌ ቦታው አስቀምጠዋለሁ እንጂ ጠዋት ከንቅልፌ ስነሳ ሳሎን ቤት ውስጥ ያቺ ወንበር እንደዛ ሁና ላያት አልፈልግም ይህ የሁልጊዜ ማታ ማታ ልምዴ ነው 

2) ከስራም ይሁን ከዋልኩበት ስመለስ ሌላው ልምዴ ደግሞ መጀመሪያ አርጊያቸው የዋልኩትን ጌጣጌጦቼን ማውለቅ, ፀጉሬን ማበጠር እና ማስያዝ ከዛ ልብሴን መቀየር ነው. ምንም ነገር አይቀርም ጆሮ ጌጥ ያንገት ጌጥ ሰዓት አንባር ሁሉ ነገሬ ወልቆ እያንዳንዱ እቃ የየራሱ ቦታ ይቅመጣል።  ሁሌ የማደርጋቸው የማልቀያይራቸው ነገሮች ለምሳሌ የጋብቻ ቀለበት ሰዓቴ እና ከጄ የማይወልቅ አንባር አለ እነዚህን ፊትለፊት dressing table ላይ የራሱ ማስቀመጫ ዕቃ አለው. ስለዚህ እዛው ላይ ነው የሚቀመጠው ለምን? ነገ ጠዋትም ከዛው ላይ ስለማነሳው ሌላ የምቀያይረው አይነት ነገር ከሆነ ግን አሁንም መልሼ እዛ የማስቀምጥበት ቦታ ነው እንጂ የማደርገው እንዲሁ dressing table ላይ ቁጭ አላደርግርውም. በምንም ተአምር አይመቸኝም.

3) ልብሴንም ስቀየር እንደዚሁ መልሼ ቦታው ላይ እሰቅላለሁ ታጥፈው የሚገቡትም ታጥፈው ይገባሉ እንጂ አልጋ ላይ ወይም ወንበር ላይ አልተዋቸውም ስለዚህ ለማታ ወይም ለነገ ተዝረክርኮ የማየው ነገር የለኝም እና ይሄ ከልጅነቴ ጀምሮ practice የማደርገው ነገር ስለሆነ ጥሩ ልምዴ ነው.

4) ልክ እንደዚህ ደግሞ organize አድርጌ የማስቀምጣቸው ነገሮች አንድ እንደ ጥሩ ልምድ ብነግራችሁ የኢሜይሌ ፍይል አደራረግ ነው. የኢሜይል ሳጥኔ እያንዳንዱ ነገር folder አለውለያንዳንዱ ከምፈልጋቸው እና ብዙ ከምፃፃፋቸው ሰዎች ጋር የራሳቸው folder አላቸው ስለዚህ ዝም ብዬ inbox ውስጥ አልተዋቸውም ካነበብኩአቸው በኃላ በሙሉ ሰብስቤ እዛ ፎልደራቸው ውስጥ ነው የሚከተቱት ስለዚህ ልክ እንደሱ ኢሜይሌንም ብታዩ አያንዳንዱ ብዙ correspondence ያለኝ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ጋር የራሳቸው folder አላቸው

5) ልክ እንደዚሁ ስልኬ ላይ፣ ወይም google ላይም የማነሳቸውን ፎቶግራፎች ( ፎቶ ግራፍ በጣም ማንሳት እወዳለሁ) በሙሉ እንደየጉዳያቸው album አደርግላቸዋለሁ አንድ አይነት ነገሮችን አንድ ላይ መሰብሰ ማለት ነው። አሁን ለምሳሌ ብዙ ጊዜ ለስራ ብዙ ፎቆች እወጣለሁ እና አዲስ አበባን ከፎቅ ላይ ማየት በጣም ነው የሚያስደስተኝ ለዚህ በሁሉም አቅጣጫ ፎቶ አነሳለሁኝ እና እነዛን ፎቶዎች በሙሉ ሰብስቤ አዲስ አበባ የሚል folder አለኝ እዛ ውስጥ አደርገዋለስለዚህ ስለ አዲስ አበባ ወይም ስለ city ስፈልግ እዛ ውስጥ ነው የማገኘው

6) ሌላው ደግሞ ቢሮዬ ውስጥ ነው። ቢሮዬ ውስጥ የተለያዩ subjects ከተለያዩ ሰዎች ጋር አወራለሁ. ስለ interior design ከሆነ የማወራው አንድ notebook አለኝ ስለ interior design ብቻ የምፅፍበት። interior design በሚመለhከት ስብሰባ ሲኖረኝም ሆነ አዳዲስ ሃሳቦቼን አሰፍርበታለሁ። እንዲሁም ደግሞ ስለ event የምፅፍበት ሌላ ኖትቡክ አለኝ። property management እንዲሁ የራሱ አለው። እና ደግሞ ሁልጊዜ አንድ በቦርሳዬ የምይዘው ምንም idea ሲመጣልኝ ወይም አንድ ነገር አይቼ designኑን ብወደው ወይንም እንዳረሳው የምፈልገውን ነገር ሲኖር የምፅፍበት note book አለኝ። አስቡት እንግዲህ ስልኬ በጣም smart ነው። Technology በጣም ነው የምወደው። ግን በጄ የምፅፈውን ነገር አልረሳውም ስለዚህ ሁልጊዜ notebook መያዝ እወዳለሁ። አንዱን ከአንዱ ጉዳይ ጋር ላለመቀላቅል ደግሞ የሄን አይነት መንገዶችን እጠቀማለሁና ለራሴ መልካም ልምዶች ናቸው ብዬ ስላሰብኩ ለውድ ዘበናይ ወዳጆቼ ላካፍላችሁ ብዬ ነው። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።

በእርግጥ የዘረዘርኳቸው ነገሮች ሁሉ obvious (ግልፅ) የሆኑ ነገሮች ቢመስሉም፣ እመኑኝ እንደ እለት ተዕለት ልምድ ተደርገው እንተርገብራቸዋለን ነው ትልቁ ነገር። ዋናው ቁምነገር ማወቅ ብቻ ሳይሆን ልምዳችን እናርጋቸው ለማለት ነው።

ይጠቅማቸዋል ለምትሉት ሁሉ share እንዲታደርጉትና እናንተም እስከመጨረሻ ፅሁፌን አንብባችሁት ከሆን አስተያየታችሁን በፅሁፍ ወይም like በማድረግ ብትገልጹልኝ በጣም ደስ ይልኛል።

የእናንተንም ጠቃሚ ልምድ ብታካፍሉኝ በጣም ደስ ይለኛል። ጊዜያችሁን ሰጥታችሁ ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ።

"የእለት ተዕለት ልማዶቻችን ነገ የምንሆናትን ሴት ቀራፂዎች ናቸው። በንቃት እንኑር።"ዘበናይ (በሰሎሜ ዳኛቸው)

#Zebenay #LifeHabits #ElegantLiving #SalomeDagnachew #PersonalBranding #EthiopianWomen #MindfulLiving

Comments

Popular Posts