አምስት የማእድ ቤትን ዲዛይን ለማድረግ የሚጠቅሙ እቅዶች፦
የማዕድ ቤት ዲዛይን ከማረጋችሁም ሆነ ከማስደረጋችሁ በፊት በቅድሚያ ልትገነዘቧቸው የሚገቡ አምስት ነገሮች፤
በመጀመሪያ፤ ምን ያህል ገንዘብ ለማውጣት ፍቃደኛ ናችሁ? ለዚህ ኘሮጀክት የመደባችሁትን በጀት በግልፅ ለዲዛይነራችሁ ለመንገር ፈቃደኛ መሆን ያስፈልጋል።
ምክያቱም ዲዛይነሩ በጀታችሁን ካወቀ በበጀታችሁ መጠን ዲዛይን ለማድረግና ለእቃ ግዢም ሆነ ለማስሪያ ከተመደበው ገንዘብ በላይ እንዲያወጣ እንዲጠነቀቅ ይረዳል።
ሁለተኛ፤ ይኼንን የማዕድ ቤት ዲዛይን ለአዲስ ቤትም ይሁን ለማሳደስ ምን ያህል ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታስባላችሁ?
በማዕድ ቤት ዲዛይን ላይ ብዙ የስራ ልምድ ያላቸው ዲዛይነሮች ምን ያህል ጊዜ እንደሚፍጅ ጥሩ ሀሳብ ሊሰጡ ያችላሉ።
ሶስተኛ፤ የራሳችሁ ወጥ ቤት ምን አይነት አቀማመጥ ቢኖረው ተመርጣላችሁ?
ያቀዳችሁት ነገር አለ? በተቻላችሁ መጠን ለዲዛይነሩ ብዙ መረጃ ብትሰጡት ይጠቅማል። ስለዚህ በቅድሚያ ለራሳችሁ ይመቸኛል፣ እወደዋለሁ የምትሉትን አይነት ኘላን ለማግኘት ብዙ ምርምር ማረግ ያስፈልጋችኃል። ለዚህ የሚረዱ የተለያዩ የማዕድ ቤት ስዕሎች፣ የማዕድ ቤት ዕቃ ካታሎጎች ማየት ይጠቅማል። በተጨማሪ የማዕድ ቤት ምርት የሚሽጡባቸው ሱቆችና ኢንተርኔት ላይ ተመልከቱ። ከነዚህ ያገኛችሗቸውንና ቀልባችሁ የወደደውን ከመፅሄት ከሆነ ከርክማችሁ አውጡ፣ ከኢንተርኔት ከሆነ ክሊኘ አርጋችሁ አስቀምጡት፣ ማስታወሻ ያዙ። ያጠረቃቀማችሗቸውን ስዕሎች ልክ እንደ ካታሎግ ለራሳችሁ አዘጋጁ፣ ያዛጋጃችሁትን የራሳችሁን ካታሎግ ለዲዛይነራችሁ አሳዩ። ዲዛየነሩ ተጨማሪ ጥያቆዎች ሊጠይቅችሁ ይችላል። ጥያቄዎቹንም በዝርዝር ፅፍችሁ ያዙ።
አራተኛ፤ ዲዛይነራችሁ መጀመሪያ ስተገናኙ አንድ ሊጠይቃችሁ የሚችለው ነገር ወጥ ቤታችሁን እንዼት ትጠቀማላችሁ? ለማብሰያ ብቻ ውይስ ለመመገቢያ ጭምር፣ የሚል ይሆናል። ለዚህ ጥያቄ ዝግጁ መሆን ያአፈልጋል። አንድውም ዲዛይነሩ ጋር ከመገናኘታችሁ በፊት እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎች ለራሳችሁ መመለስ አለባችሁ።
ምሳሌ፦ ከቤተስብና ጓደኛ ጋር ከቤት ውስጥ ብዙ ትዝናናላችሁ?
ቤተስቦቻችሁ ጋር በስራ ቀናት በቤት ወስጥ ብዙ ታሳልፋላችሁ ወይም በዕረፍት ቀናት ብቻ ነው?
በነዚህ ውስኔዎች ውስጥ የቤተስብ አባላትም አስተያየት ቢሰጡበት መልካም ነው።
አምስተኛ፤ የማዕድ ቤታችሁን ዲዛይን ለማስደረግ እንዼት መዘጋጀት እነደሚቻል በማዕድ ቤቱ ዲዛይን ኘሮጀክት ምክንያት ለሚፈጥሩ ማንኛውም አይነት እክሎች ራስን ማዘጋጀት ያስፈልጋል። ይሁን እንጂ ትክክለኛ ዕቅድ በቅድሚያ ማውጣትና በታቀደው መሰረት ኘሮጀክቱ በተቻለ ፍጥነት እንዲከናወን ማድረግ ይቻላል።
ማጠቃለያ
ወጥ ቤት ዲዛይን ለማረግ ምንም ነገር ከመወሰን በፊት ዲዛይኑ ሰኬታማ እንዲሆን በጥሞና የታሰበበት ዕቅድ ማውጣት አስፈላጊ ነው።
ጥሩ የማዕድ ቤት ዲዛይነር ዲዛይን የሚያረግለትን ሰው (የባለቤቱን) ፍላጎቶች በደንብ መረዳትና እንደሚመቸው አርጎ በበጀቱ ልክ መስራት አለበት።
ቁልፍ ቃላት
የማዕድ ቤት ዲዛይን /ንድፍ ፣ ማዕድን ቤት ፣ ወጥ ቤት remodelling.
#kitchendesign #Baroqueinethiopia #kitchen #interiordesign #kitchendecor #homedecor #design #interior #kitchenremodel #home #homedesign #architecture #kitcheninspiration #kitchenrenovation #decor #interiors #kitchenset #homesweethome #interiordesigner #renovation #furniture #kitchenisland #kitchenideas #kitchengoals #kitchencabinets #kitchens



Comments
Post a Comment