መስታወት የሳሎን ጠረጴዛ


ከጥቂት አመታት በፊት የመስታወት የሳሎን ጠረጴዛ ያላቸው ስዎች ሀብታምና የጥሩ ዕቃ አዋቂዎች መካከል ይታሰቡ ነበር። ለዚህም ነበር በአለማችን ውስጥ የመስታወት የሳሎን ጠረጴዛ በጣም ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ ሊገኙ የሚችሉት። ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ነገሮች ተቀያይረዋል።

በአሁኑ ጊዜ ማንም ሰው የመስታወት ጠረጴዛ ሊኖረው ይችላል ምክያቱም አሁን ማንም  ብዙ ገቢ የሌለው ሰው እንኳን በተመጣጣኝ ዋጋ ሊገዛው እና ሀብታሞቹ ይገዙት በነበረው አይነት እቃ ቤቱን ማሳመር ይቻላል።

ድሮ የመስታወቱን ጠረጴዛ ውድ የሚያደርገው በናስ የተሰራው መስታወቱን የሚይዘው ፍሬም ስለነበረና ናስ ደግሞ ወድ ስለነበር ነው. የሀስ ፍሬም ያለው ጠረጴዛ ለማንኛውንም አይነት ክፍል ግርማ ሞገስና ውበት ይጨምርለታል። እንደነዚህ አይነት ውድ እቃዎች ከወላጆች ወደ ልጆች ሊተላለፉ የሚችሉ ምርጥ የቤት እቃዎች ናቸው 

 

በእርግጥ ህፃናት ያሉበት ቤት ውስጥ መስታወቱ እንዳይሰበር ሊያስጋ ይችላል። እንደዚህ አይነት ልዩ የመስታወት ዕቃዎች መግዛት አንዱ ችግር ይኼ ነው። ከመሰበሩ ሌላ የጣት አሻራዎችን ከመስታወቱ ለማፅዳትም ሌላው ትልቅ ስራ ነው።  ሆኖም የመስታወት የሳሎን ጠረጴዛ ጊዜ ከማይሽራቸው የቤት ቁሳቁሶች የተሻለ ሆኖ ይታያል። እንዲሁም ለማንኛውም አይነት የዲዛይን እስታይልም ይስማማል።

 


 

               




Comments

Popular Posts