ቤታችን ማንነታችንን ይናገራል
እስኪ የቤታችሁን ውስጣዊ ገጽታ ዞር ዞር ብላችሁ ቃኙና ምን ያህል ከእናንተ ጥ ብ ለቤታችን የምንመርጣቸው የቤት ማሳመሪያ ቁሳቁስ፣ ጌጦችና የቤት ቀለማት ስለ ባሕርይያችን ብዙ ነገር ሊገልጹ ይችላሉ።
ከሰው ቤት ብዙ ነገሮችን መረዳት ይችላል። ቤታችንን የምናስጌጥበት መንገድ፣ የምንመርጣቸው ዕቃዎች፣ የባህረያችንን የተለያዩ ገፅታዎች ሊጠቁሙ የችላሉ። ቤታችንን የምናሳምርበት ዕቃ አይነቱና አቀማመጡ የግል ማንነታችንን አመለካከታችንና ስሜታችንን በግልፅ ያንፀባርቃል። ስለዚህ ቤታችን የአኗኗር ዘይቤያችንን የሚያንጸባርቅ መሆኑን ማረጋገጥህ አስፈላጊ ነው።
አንድ ሰው፣ ቤቱ ውስጥ ባሉት ዕቃዎች አማካኝነት ባሕርይውን ማንጸባረቅ የሚችልባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ ። ስለ አንድ ሰው ማወቅ የምትችሉበት አንዱ መንገድ ስለ ተሞክሮዎቹ ማወቅ ነው። ብዙውን ጊዜ እነዚህን ነገሮች በቤት ውስጥ ማየት ይቻላል። በጉዞ ላይ ብዙ ጊዜ የሚያሳልፉ የቤት ባለቤቶች ብዙውን ጊዜ ከተለያዩ አገሮች ገዝተውም ሆነ በስጦታ ያገኙአቸውን ጌጣጌጦች ወደ ቤታቸው ይዘው በመምጣት በሕይወታቸው ውስጥ ያጋጠሟቸውን ተሞክሮዎች ያሳያሉ። በግድግዳው ላይ ያሉት ሥዕሎች ወይም መጋረጃዎቹ በቀላሉ ግለሰቡ ለእንስሳት ወይም ለአበባ ያለውን ፍቅር ሊያንጸባርቁ ይችላሉ።
በአኗኗር ዘይቤአቸው የተረጋጉ እንዲሁም ነገሮችን እቅድ ማውጣት የሚፈልጉ ሰዎች መደራጀት/organize መሆን የሚወዱ ቤታቸው ሁልጊዜ ትክክል፣ የተዘጋጁ ንጹህና ሰፊ ናቸው።
ተፈጥሮአዊ ነገር የሚወዱ ሰዎች ቤቶች በዕፅዋትና በአበቦች የተሞሉ ይሆናሉ።
በመፅሀፍት ፣ በኢንሳይክሎፒድያዎች የተሟላ ቤት፣ የማወቅ ጉጉት ያለው ብዙ የሚያነብ ሰው ቤት መሆኑን እንድንገነዘብ ያስችለናል።
በፋሽን መፅሄቶች ወይም በፊልሞች፣ የሀይማኖት መግለጫ ቁሳቁሶች የተሟላ ቤት፣ እንደዚሁ ፋሽን ተከታይ ወይም ሀይማኖተኛ ሰው ቤት መሆናቸውን ይናገራል።
በሌላ በኩል ደግሞ በጣም አነስትኛ የቤት ቁሳቁስ ያለበት ቤት ተግባራዊ መሆንን ከሚወዱና አላስፈላጊ የሆኑ ብሎ የሚያስባቸውን ነገር ሁሉ የሚያስወግድ ሰው ጋር ሊጣመር ይችላል።
አንዳንድ ቤቶች በተለያዩ የተዋቡ እና በጣም ውድ እቃዎች ቢሞሉም የቤቱን ባለቤቶች ባህሪ የሚወክሉ ስላልሆኑ ባለቤቶቹ ራሳቸው ለእንግድነት እዛ ቤት ውስጥ ያሉ እንጂ ባለቤቶች አይመስሉም። እንደውም ቤቱ የግል መኖርያ ቤት መምስሉ ይቀርና ቆንጆ የቤት እቃ መሽጫ ሱቅ ይመስላል።
ይሁን እንጂ ከሁሉ የበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር ቤትን ከልብ መገንባት ነው ቤታችን የእንግዳ ተቀባይ ስሜት ከመፍጠር በላይ ለእኛ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸውን እንግዶቻችንን የምናስተናግድበት ቦታ እንደመሆኑ በህይወታችን ውስጥ ግሩም የሆኑ ወቅቶችን ለማሳለፍ የሚያስችለን አቅም እንዲኖረው አርገን መገንባት ይኖርብናል ።
እዚህ ላይ መገንባት ስንል ህንፃውን ሳይሆን ውስጡን በማንነታችን ስንሞላው ማለት ነው። እያንዳንዱ ትንሽም ሆነች ትልቅ ፤ ውድም ሆነ እርካሽ፤ የእኛ ብለን በየጊዜው ወደ ቤታችን አስገብተን ንብረታችን ያረግነው ሁሉ የእኛን ማንነት መገለጫ እንደመሆኑ ወደ ቤታችን ይዘን የምንገባው፣ ገንዘባችንን የምናጠፋበት ነገር ሁሉ ትክክለኛ ምርጫችን መሆን አለበት። አለበለዚያ ምንም ጥቅም የሌለው ኮተት ከመሆን በስተቀር ትርጉም የለውም። በአንፃሩ፣ ቤታችን በምንወዳቸውና በምንፈልጋቸው ውይም በሚያስፈልጉን ቁሳቁሶች ስናሳምራቸው፣ ቤቱን የምንወደው ቤት እንዲሆንና ሁሌም ተመልስን እንድንሄድበት የምንናፍቀው ቦታ ይሆንልናል። በተለይም አንድ ሰው ወደ ቤታችሁ ገብቶ እናንተን እንደሚወክል በእርግጥ ሊሰማው መቻሉ ደግሞ በጣም አስደሳች ነው።

Comments
Post a Comment