መጋረጃዎች

 መጋራጃ ወደ ቤት ውስጥ የሚገባን ብርሃን ለመቆጣጠርና የቤታችን ውስጥ አድማቂ አንዱ አካል ነው፡፡ መጋረጃ ከመምረጥ የበለጠ ከባዱና ጥንቃቄ የሚፈልገው ትክክለኛ ልክ መውሰድ ነው፡፡ አለካከችን ከመስኮታችን ሥፋት በለጥ ያለ መሆን አለበት ይሄ ዘዴ መጋረጃውን ወደ ጎን በምንሰበሰብበት ጊዜ የተሰበሰበው ጨርቅ የተወሰነውን የመስታወት ክፍል ከመሸፈን ይልቅ በደንብ ወደ ጥግ ለማምጣት ይረዳናል፡፡ የመጋረጃ ጨርቅ አመራረጣችንም ቢሆን ሌላውን ቤት ውስጥ ያለ ዕቃ ማገናዘብ ይኖርብናል፡፡ ወፍራምና ከበድ ያሉ የመጋረጃ ጨርቆች ክፍሉን ጨለም ለማድረግ እንዲሁም በመስታወት የሚገባን ቅዝቃዜ ለመቀነስ ይረዳሉ፡፡ ስስና ምንም አይነት ንድፍ የሌላቸው መጋረጃዎች ደግሞ ብርሀንን ለማስተላለፍ ይረዳሉ።

 

መጋረጃዎችን  ከመምረጣችሁ በፊት ማውቅ ያለባችሁ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች ፦

 1. የመጋረጃውን ጨርቅ ከመግዛታቸው በፊት ከመጋረጃ መሽጫ ሱቅ ትንሽ ቁራጭ ወደ ቤት አምጥታችሁ ቤት ውስጥ ካሉ ዕቃዎች ጋር አስተያዩ። ማስታውስ ካለባችሁ ነገሮች አንዱ በቤታችሁ ውስጥ ባለው ጌጣጌጥ ውስጥ እንዴት ማካተት እና እንዴት ልትጠቀሙበት እንደምትችሉ ነው።

 

2. የተዘበራረቀ መልክ እንዳይኖር የመጋረጃና ሌሎች እንደ ሶፋና የሶፋ ትራሶች የለበሱትን ጨርቅ መልክ ማመሳሰል።


  

3. በመጀመሪያ, ብዙ የተለያዩ የውስጥ ንድፍ ዓይነቶች(interior design styles) መኖራቸውን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ለምሳሌ ንድፍ ያላቸው የመጋረጃ ጨርቆች ክላሲክ የሆነ ስታይል ላላቸው ክፍሎች ያምራሉ።

 

4. ብዙ ስዕሎች፣ የተለያዩ ደምቅ ያሉ ቀለም ያላቸው ግድግዳዎች፣ ወይም የቤት ዕቃዎች ባሉባቸው ክፍሎች ውስጥ አንድ አይነት ቀለም ብቻ ያለውና ዝም ያለ ቀለም ያለው መጋረጃ መምረጥ ይሻላል።

 

5. ቬኒቨያን ብላይንድስ በቁመት ወይም በአግድም በተደረደሩ በተፈለገው በአንግል ብርሀን ለማስገባት ሊያጨልም የሚያስችሉ መጋረጃ አይነቶችም አሉ።

 

6. የአልጋ ልብስ ፤ አንሶላ፣ የጠረቤዛ ጨርቅ እና ፎጣዎች ከመጋረጃ ጨረቃች ጋር ለጌጥነት ያገለግላሉ።

 

   ማጠቃለያ

መጋረጃ ርዝመት:- በምንም ዓይነት መንገድ አጭር  መጋረጃ ወይም መስኮቱ  ላይ ድረስ የቀረ መጋረጃ ውበት የለውም ቢያንስ ቢያንስ መሮቱን እስኪነካ ወደታች በግድግዳው ግርጌ ድረስ መሆን አለበት፡፡

የመጋረጃ ጨርቅ:- ስትገዙ በርከት አርጋችሁ ግዙ፡፡መጋረጃ ብዙ ን ቢኖረው ስረሚያምር ቢያንስ ከመስኮታችሁ ስፋት 2.5% ጊዜ በላይ ተጨማሪ ጨርቅ ይፈልጋል፡፡

የመጋረጃ አሰቃቀል፡- መጋረጃ ስንሰቅል ከላይ ከመስኮታች ጫፍ ከ10-15 ሴ.ሜትር ብለን መሆን አለበት ፡፡ ይህ በተለይ ትንሽና አጭር መስኮት ያለውን ቤት ሰፊና ረጅም ስለሚያስመስለው ውበት ይጨምርለታል፡፡

 

የመስኮቱን አስራር፣ ስፋት፣ ርዝመት፣ ቅርፅ፣ ስለ ክፍሉ መጠን፣ ክፍሉ ለምን ጥቅም እንደሚውል፣ ውስጥ ካሉ ጨርቅ የለበሱ እቃዎች ጋር መጋረጃው እንዲሰጥ የተፈለገው አገልግሎት፣ አስቡ። መጋረጃዎችን በጣም በተለያዩ መንገዶች ሊስቀሉ የችላሉ። ምንም ጌጥነት የሌላቸው የመጋረጃ ዘንጎች ቢኖሩም አንዳንድ ዘንጎች ለጌጥነትም የሚውሉ አይነቶች ናቸው። ትክክለኛ የመጋረጃ ዘንግ መምረጥ የክፍሉን ውበት ይጨምርለታል።

For any inquiry please contact us via

salome@baroqueinethiopia.com 



Comments

Post a Comment

Popular Posts